ይህ የአማራ ትሥሥርር በቻይና ይፋዊ ድረ-ገጽ ነው። በዚህ ድረ-ገጽ የአማራን ሕዝብ ታሪክ፣ ሃይማኖት፣ ባሕል፣ ልማድ፣ አርበኝነት፣ ቅርስ እና ሌሎች ተዛማጅ ጉዳዮችንም ጭምር ለአባላት በሚገባ እናሳውቃለን። የድረ-ገጹ ዋና አላማ የአማራን ታሪክ በሚገባ ለሁሉም በማስተማር ታሪካችንን ወደቀደመ ልዕልናው መመለስ ነው። አንድ አማራ ለሁሉም አማራ፤ ሁሉም አማራ ለአንድ አማራ፤ አንዲት ነጻ ሃገር ኢትዮጵያ -->

አጤው የነገሡበት ዕለት

ጥቅምት 25 ቀን - አጤው የነገሡበት ዕለት

ጥቅምት 25 ቀን 1882 ዓ/ም እምዬ ምኒልክ ሞዓ አንበሳ ዘእምነገደ ይሁዳ ምኒልክ ንጉሠ ነገሥት ዘ ኢትዮጵያ ተብለው የነገሡበት ዕለት ነው። የንግሥናውን ሁነት ጋዜጠኛ እና ደራሲ ጳውሎስ ኞኞ አጤ ምኒልክ(መጽሐፉን ለማግኘት)  በተሰኘው መጽሐፋቸው እንደሚከተለው ገልጸውታል።

… የንግሡ በዓል በ1882 ዓ/ም ጥቅምት 25 ቀን አዲስ አበባ እንዲሆን ተወሰነ። ምኒልክም በዋዜማው ጥቅምት 24 ቀን እንጦጦ ማርያም ቤተክርስቲያን ሂደው አደሩ። ሌሊቱኑ ሥርዓተ ንግሡ ተጀምሮ ዘጠኝ ሰዓት ሲሆን ጳጳሱ የወርቅ ሰይፍ ባርከው አስታጠቋቸው። ከዚያም በወርቅ ሽቦ የታሸቡ ሁለት ጦሮች አስያዟቸው። ቀጥለው የወርቅ ዘንግ ሰጡዋቸው። ይህ ሁሉ ከሆነ በኋላ ቅብዐ መንግሥቱን ተቀብለው የወርቁን ዘውድ ጳጳሱ ደፉላቸው። 

ድግሱን እና አጠቃላይ ድባቡን አስመልክቶ ፀሐፌ ትእዛዝ ገብረ ሥላሴ ታሪክ ዘመን ዘ ዳግማዊ ምኒልክ ንጉሠ ነገሥት ዘኢትዮጵያ በተሰኘው መጽሐፋቸው እንዲህ ይላሉ።

… ራሶች ባለወርቅ ቀሚስ ለብሰው፣ ባለወርቅ ለምድ ደርበው፣ ራስ ወርቅ አስረው፣ ባለወርቅ ጋሻና ጠብመንጃ ይዘው ግራና ቀኝ ሆነዋል። ሊቀ መኳሶችም ከፈይ ቀሚስ ለብሰው፣ካባ፣ ላንቃ ደርበው በንጉሠ ነገሥቱ ፊት እና ኋላ ሆነዋል።

ቀጠል ያደርጉና ይኼንን ይላሉ። … ሰይፈ ጃግሬዎች በንጉሠ ነገሥቱ ግንባር ባለው ርቀት ሰይፍ ይዘው ተሰልፈዋል። የእልፍኝ ዘበኞችም እንደ ግምጃ አጥር ዙሪያውን ገጥመውታል። ሊጋባው ባለወርቅ ቀሚስ ለብሶ፣ ለምድ ደርቦ፣ ከንጉሠ ነገሥቱ የወርቁን ዘንግ ተቀብሎ በግምጃ ሸፍኖ ይዞ ከሰይፈ ጃግሬዎች ኋላ፣ ከሊቀ መኳሶች ፊት ይኼድ ነበር። መነኮሳቱም ልብሰ ክህነታቸውን ለብሰው በፊት በኋላ፣ በቀኝ በግራ ሁነው ( ሆነው)ዙሪያ ገባውን ያጥናሉ።

 እኒሁ ጽሐፊ በዚሁ መጽሐፋቸው ወረድ ብለው  እንዲህ ይላሉ:-  የዳሱ ጌጥ፣ በዙፋናቸው ላይ የተዘረጋው የወርቅ ምንጣፍ፣ የወርቁ መከዳ የእንቁጣጣሽ አበባ ይመስል ነበር። ከዚህ በኋላ መሶብ መግባት፣ ጠጅ መስጠት ተጀመረ።ጠጁን እንደልማዱ ባሸንዳ ይፈሳል። ነገር ግን በዚህ ዘመን ከብት አልቆ ነበርና ( ያኔ የከብት ድርቅ እና በሽታ መከሰቱን ልብ በሉ) የሥጋ ነገር ጥቂት አጠር ይላል።


መውጫ:- ታሪኩን የማያውቅ ትውልድ ሥር አልባ ተክል ነው ( Marcus Garvey)

አዘጋጅ፦ የታሪክ ክፍል


የአማራ ትስስር በቻይና

ጥቅምት 25  2015 ዓ.ም 

ቻይና

የአማራ ትስስር በቻይና(ANiC)

የአማራ ሕዝብ የሚያኮራ ታሪክ፣ ቋንቋ፣ ስነጽሑፍ፣ ሃይማኖትና ባህል ያለው፤ የተፈጥሮ እና ሰው ሰራሽ ቅርሶች ባለቤት የሆነ፤ ሃገር የሰራ፣ ነጻነቱን ያስጠበቀ፤ የራሱ የሆነ ፊደል ያለው፤ የጥንታዊ ትምህርት ስርዓት ባለቤት የሆነ ጀግናና ኩሩ ሕዝብ ነው። የአማራ ሕዝብ በሃገረ መንግስት ምስረታ ሃገርን ከወራሪ መጠበቅና ዳር ድንበሯን በማስጠበቅ ታላቅ ገድል በመስራት እኛ ልጆቹ ቀና ብለን እንድንሄድ አድርጎናል።

Post a Comment

ቀዳሚ ገጽ ተከታይ ገጽ
hi