Home የቴክኖሎጂ ክፍል (Department of Technology) byየአማራ ትስስር በቻይና(ANiC) -4/06/2022 09:07:00 PM 0 የቴክኖሎጂ ክፍል የቴክኖሎጂ ክፍል በአማራ ትስስር በቻይና (ANiC) ከተመሰረቱ ስድስት ክፍላት ውስጥ አንዱ ሲሆን የተመሰረተበት ዋና አላማ፦ ፩. ለታሪካዊ ሰነዶች እና ለተለያዩ መረጃዎች ማስቀመጫ የሚሆን ድህረ-ገጽ ማዘጋጀት(እንዲዘጋጅ ማድረግ) እና የተሰራውን ድህረ-ገጽ መቆጣጠር ፪. አዳዲስና ጠቃሚ የሆኑ ቴክኖሎጂዎችን ለስብስቡ አባላት ማስተዋወቅ ፫. ለህዝባችን የሚጠቅሙ ፕሮጀክቶችን አባላትን አሳታፊ ባደረገ መልኩ መንደፍና መስራት አባላትም እንዲሰሩ በበላይነት መምራት ፬. ማህበራዊ ሚዲያ ላይ የሚደረጉ ዘመቻዎችን ከመረጃ ክፍል ጋር በመነጋገር አባላቱን ማሳተፍ ፭. በስብስቡ ወስጥ ለሚገኙ አባለት የ "WorkShop" ሥልጠና መስጠት ምንም እንኳን ከላይ የተጠቀሱትን ዐቢይ እቅዶችን ይዞ የሚንቀሳቀስ ክፍል ቢሆንም በስብስቡ አባላት እንዲሁም በትስስሩ የሥራ አስፈጻሚዎች የሚቀርቡ ክፍሉን የሚወክሉ ሌሎች ሥራዎችን ትኩረት ስጥቶ የሚሰራ ክፍል ነው። ክፍሉ ማንኛውም የስብስቡ አባል ከቴክኖሎጂ ጋር ግንኙነት እና ልምድ እንዲኖረውም በአጽንኦት ይሰራል። Facebook Twitter