እስካሁን የተከናወኑ ዋና ዋና ስራዎች በዝርዝር
ክፍላችን የተሰጡትን ዋና ዋና እቅዶች ይዞ ሥራዎቹን በአግባቡ እያከናወነ ይገኛል። ከነዚህ እቅዶች አንዱ እና ዋነኛው በዋና እቅዳችን ተራ ቁጥር ፩ በተገለጸው መሰረት
ለታሪካዊ ሰነዶች እና ለተለያዩ መረጃዎች ማስቀመጫ የሚሆን ድህረ-ገጽ ማዘጋጀት(እንዲዘጋጅ ማድረግ) እና መቆጣጠር የሚለውን ይዞ አባላትን አሳታፊ ባደረገ መልኩ እየሰራ ይገኛል። እስካሁን ባለው ጊዜ ውስጥ ድህረ-ገጹ የሚያስፈልግበትን ዋና ዋና አላማዎች፤ የሚያስፈልጋቸውን ክፍላት እንዲሁም በቀዳሚ ገጹ ላይ የሚጻፉ ዋና ዋና ጽሁፎችን የሥራ አስፈጻሚዎችን እንዲሁም የተለያዩ አባላትን(የክፍሉን አባላት ጨምሮ)በማነጋገር መረጃዎችን እያሰባሰባ ሥራዎቹን በመስራት ላይ ይገኛል። ለመረጃ ይሆን ዘንድ ማቅረቡ አስፈላጊ ከሆነ ድህረ-ገጹ ተሰርቶ ሲጠናቀቅ ወደ አባላት ለማሰራጨት የ "Domain name" ግዢ ስለሚያስፈልግ ግዢ ከመፈጸማችን በፊት ነጻ የሆኑ እንደ "
Blogger(ብሎገር)"፣ "
ብሎግስፖት(Blogspot) "፣ "
ወርድ ፕሬስ( Word-press" እና ሌሎችን ተጠቅመን ለአባላት እንደ ምሳሌ ማሳየቱ አስፈላጊ ሆኖ ተገኝቷል። ከላይ ከተዘረዘሩት ውስጥም
ብሎግስፖት(Blogspot) መርጠን ድዛይኑን ጨርሰን የአባላት ወርሀዊ ስብሰባ ላይ ለማሳየት ዝግጅታችንን አጠናቀናል። ድዛይኑን ካዩ በኋላ የሚሰጡት አስተያየት ካላ
በዚህ አድራሻ መልእክት ቢጽፉልን ፈጣን ምላሽ እና ማስተካከያ የምናደርግ መሆኑን ለመግለጽ እንወዳለን።
Department of Technology