ይህ የአማራ ትሥሥርር በቻይና ይፋዊ ድረ-ገጽ ነው። በዚህ ድረ-ገጽ የአማራን ሕዝብ ታሪክ፣ ሃይማኖት፣ ባሕል፣ ልማድ፣ አርበኝነት፣ ቅርስ እና ሌሎች ተዛማጅ ጉዳዮችንም ጭምር ለአባላት በሚገባ እናሳውቃለን። የድረ-ገጹ ዋና አላማ የአማራን ታሪክ በሚገባ ለሁሉም በማስተማር ታሪካችንን ወደቀደመ ልዕልናው መመለስ ነው። አንድ አማራ ለሁሉም አማራ፤ ሁሉም አማራ ለአንድ አማራ፤ አንዲት ነጻ ሃገር ኢትዮጵያ -->

About ANiC

መግቢያ

በዚህ ማኅበር አማራ ስንል በክልሉ ውስጥና ከክልሉ ውጪ የሚኖርን የአማራ ህዝብ ያካትታል። የአማራ ሕዝብ የሚያኮራ ታሪክ፣ ባህል፣ ቋንቋ፣ ስነጽሑፍ፣ ሃይማኖትና ባህል ያለው፣ የተፈጥሮ እና ሰው ሰራሽ ቅርሶች ባለቤት፣ ሃገር የሰራ፣ ነጻነቱን ያስጠበቀ፣ የራሱ የሆነ ፊደል ያለው፣ ጥንታዊ የትምህርት ስርአት ባለቤት፣ የሆነ ጀግናና ኩሩ ሕዝብ ነው። የአማራ ሕዝብ በሃገረ መንግስት ምስረታ ሃገርን ከወራሪ መጠበቅና ዳር ድንበሯን በማስጠበቅ ታላቅ ገድል በመስራት እኛ ልጆቹ ቀና ብለን እንድንሄድ አድርጎናል። ይሁን እንጂ አሁን ላይ የአማራ ሕዝብ ለሃገር የዋለው ውለታ ተረስቶና እንደ ጥፋት ታይቶ በጠላትነት ተፈርጆ በየቦታው እንዲፈናቀል ሃብቱን እንዲያጣ ብሎም እንዲሞት ተደርጓል። የአማራ ጠላቶች አማራን በጠላትነት ፈርጀውና መንግስታዊ መዋቅር በመዘርጋት ለማጥፋት ሲሰሩ ኖረዋል እየሰሩም ነው። የአማራን ሕዝብ በተለይም ከክልሉ ውጭ የሚኖረውን አማራ እንደ ወራሪ በመቁጠር እንዲሞትና እንዲፈናቀል ተደርጓል። ከመግደል አልፎም ታሪካዊ ግዛቶቹንና ባህሎቹን በመዝረፍ በሁሉም አቅጣጫ ለማጥፋት ተንቀሳቅሰዋል። አማራን ለማጥፋት በመዋቅርና በመንግስት ድጋፍ ከኢህአዴግ በትረ ስልጣን ጀምሮ የአማራን ህዝብ ያለስሙ ስም በመስጠት እና የልብ ወለድ ታሪክ በመስበክ የተጠና የኢኮኖሚ፣ ማህበራዊ እና የፖለቲካ መገለል ደርሶበታል። የአማራን ህዝብ ለማዳካም ከተቻለም ለማጥፋት የሚያስችል ርዕዮተ ዓለም በመንደፍ የአማራን ሕዝብ የማጥፋት ጥንስስ የተጀመረው ግን ከዚያ በፊት ነው። የውጭ ዲፕሎማቶችና የኢጣሊያ ቅኝ ገዥዎች አማራ የእነሱን የቅኝ ግዛትና የበላይነት አስተሳሰብ ፈጽሞ እንዳልተቀበለውና እየተዋጋቸው መሆኑን ሲያውቁ ሌሎች ብሔሮች በጠላትነት እንዲያዩትና እንዲነሱበት ለማድረግ ስራ ሰርተዋል። ለምሳሌ፦ ባሮን ሮማን ፕሮቻዝካ በ1926 ዓ.ም በጀርመንኛ ቋንቋ በቪየና ከተማ ባሳተመው መጽሐፉ እንዲህ ይላል፤ “ኢትዮጵያ ውስጥ አማራ የሚባል ብሔር አለ፤ የዚህ ብሔር አካሄድ አፍሪካን ጠቅልሎ በቁጥጥር ስር ከማዋል አልፎ ለእኛ ለነጭ ዘሮች የማይመለስ ኃይል ነው፤ ይኼን አስፈሪ ብሔር እኛ ነጮች ተባብረን አስቸኳይ እርምጃ ካልወሰድን የሚያቆመው ስለማይኖር ለማዳከም መሥራት አለብን። ይኼን አስፈሪ ኃይል ለማዳከም በመጀመሪያ በኢትዮጵያ ውስጥ ያሉ የተለያዩ ብሔሮች በአማራ ሕዝብ ላይ እንዲነሱበት ፖሊሲ ቀርፀን መንቀሳቀስ አለብን” (Abyssinia the powder Barrel, p. 7) ይላል። ትህነግም እራሱን የትግራይ ሕዝብ ነጻ አውጭ ድርጅት ብሎ ሲመሰረት አማራን በጨቋኝነት በመፈረጅ ነበር። አማራው በዘውጉ የሚደርስበትን ሁሉ ችሎ የለመደውን ኢትዮጵያ እንዳትጠፉ ቢያስጠብቅም በኢትዮጵያዊነት ስም ፍላጎቱን በብሔር ብሔረሰቦች ላይ የሚጭን ጨቋኝ ህዝብ ነው እያሉ በድንጋይ መወገር የሚገባው ሃጢያተኛ ህዝብ አድርገው ያቀርቡታል። የፈጠራ ታሪክ በመስበክ በማንኛውም ጉዳይ ዙሪያ የስነልቦና ጫና በማሳደር ከፖለቲካዊ እና ማህበራዊ ተሳትፎ ማግለል እንዲሁም ሌሎች ሰፊ ግፎች እንዲፈጸምበት በማድረግ በመሰረታት ሃገር በሰላም እንዳይኖር አድርገዋል። ይህ ሁሉ ሲደረግበት ከአማራው በኩል የተሰጠው ምላሽ እዚህግባ የሚባል አይደለም። በተለይም አብዛኛው አማራ እንደ አማራ መቆም ከኢዮጵያዊነት መሸሽ ሲለሚመስለው እራሱንና ሃገሩን ለማዳን ያደረገው ጥረት የለም። ስለዚህ አማራው በዘሩ በማንነቱ በባህሉና በአጠቃላይ በእሴቱ እየደረሰበት ያለውን ጥቃት መመከት የሚችለው ከሁሉም ክፍላተ-ዓለማት በመሰባሰብና አንድ ላይ በመቆም ብቻ ነው።ከሁሉም በላይ ደግሞ እኛ ተምረናል የምንል ማንነታችን ላይ የተቃጣብንን የመጥፋት አደጋ የመታደግ አቅሙም፣ክህሎቱም፣ሀይሉም ስላለን አማራነታችን ለማስከበር በማንነታችን መደራጀት በማስፈለጉ በዚህም መነሻነት በቻይና ሃገር ቸንዱ የምንገኝ የአማራ ልጆች በመሰባሰብ ታሪካዊ እና ትውልዳዊ አደራችንን ለመወጣትና በተግባርም የመፍትሄ አካል ሆነን ለመገኘት ይህንን በቻይና የአማራ ማህበር ለመመስረት ተነስተናል:: ይህ ትስስር ልክ እንደማንኛውም ማህበራዊ ሚዲያ የመወያያ እና ለተለያዩ የአማራ ጉዳዮች የመፍትሔ ሃሳብ ማቅረቢያ ብሎም ድጋፍ ማድረጊያ ዝግ ትስስር/Network/ ነው። ስብስቡ ለአማራ ህዝብ ጥቅም የቆመ በአማራ ልጆች ብቻ የተመሰረተ ሲሆን አማራ ያልሆኑ ማንኛውም እዚህ ትስስር ውስጥ አባል መሆን አይችሉም ። ይህ ማህበር በትንሽ የአማራ ልጆች የተመሰረተ ትልቅ አላማና ራዕይ ያለው ማህበር ነው። የዚህ ማህበር ዋና አላማ አማራን ማስከበርና የአማራን ታሪክ ወደቀደመ ልዕልናው ለመመለስ የሚሰራ ስብስብ ነው።

[ሙሉ ታሪኩን በቅርብ ቀን ይጠብቁ...]

የአማራ ትስስር በቻይና(ANiC)

የአማራ ሕዝብ የሚያኮራ ታሪክ፣ ቋንቋ፣ ስነጽሑፍ፣ ሃይማኖትና ባህል ያለው፤ የተፈጥሮ እና ሰው ሰራሽ ቅርሶች ባለቤት የሆነ፤ ሃገር የሰራ፣ ነጻነቱን ያስጠበቀ፤ የራሱ የሆነ ፊደል ያለው፤ የጥንታዊ ትምህርት ስርዓት ባለቤት የሆነ ጀግናና ኩሩ ሕዝብ ነው። የአማራ ሕዝብ በሃገረ መንግስት ምስረታ ሃገርን ከወራሪ መጠበቅና ዳር ድንበሯን በማስጠበቅ ታላቅ ገድል በመስራት እኛ ልጆቹ ቀና ብለን እንድንሄድ አድርጎናል።

Post a Comment

ቀዳሚ ገጽ ተከታይ ገጽ
hi