ይህ የአማራ ትሥሥርር በቻይና ይፋዊ ድረ-ገጽ ነው። በዚህ ድረ-ገጽ የአማራን ሕዝብ ታሪክ፣ ሃይማኖት፣ ባሕል፣ ልማድ፣ አርበኝነት፣ ቅርስ እና ሌሎች ተዛማጅ ጉዳዮችንም ጭምር ለአባላት በሚገባ እናሳውቃለን። የድረ-ገጹ ዋና አላማ የአማራን ታሪክ በሚገባ ለሁሉም በማስተማር ታሪካችንን ወደቀደመ ልዕልናው መመለስ ነው። አንድ አማራ ለሁሉም አማራ፤ ሁሉም አማራ ለአንድ አማራ፤ አንዲት ነጻ ሃገር ኢትዮጵያ -->

Colonel Abdissa Aga

 ኢትዮጵያ ጀግናዊ አብዲሳ አጋ 

አብዲሳ አጋ በ ፲፱፻፲፪ ዓ.ም ዓ/ም የጣልያን ወረራ ወቅት ተማርኮ ወደ ጣልያን ከተወሰደ በኋላ ብርድ ልብሱን ቀዳዶ በመቀጣጠል በመስኮት አምልጦ በርካታ ጀግንነቶችን የፈጸመ የኢትዮጵያ ወታደር ነው። ኮሎኔል አብዲሳ አጋ የተወለደው በ1912 ዓ.ም ወለጋ ውስጥ በአሁኑ አጠራር ነጆ በምትባል  ከተማ ነው። እንደ ማንኛውም ኢትዮጵያዊ ሕጻን እድሜያቸው ለትምህርት ሲደርስ ወደ ነጆ ሚሲዮናዊ ትምህርት ቤት በማቅናት ፊደል መቁጠር ጀመሩ። ይህ ጅማሬያቸው ግን ረጅም ርቀት ሳይጓዝ ስድስተኛ ክፍል ላይ ተቋረጠ። ምክንያቱ ደግሞ ወላጅ አባታቸው ባላጠፉት ጥፋት ተወንጅለው እስር ቤት በመግባታቸው ነበር። 

             ኮሎኔል አብዲሳ አጋ

ልጅ አብዲሳ ይህ የተሳሳተ ፍርድ እውነታውን አግኝቶ አባታቸው ነጻ ይወጡ ዘንድ ትምህርታቸውን ትተው ከላይ ታች ማለት ጀመሩ። ይህ ጥረታቸው ግን ሳይሳካ ከመቅረቱም በላይ ወላጅ አባታቸውን በሞት ተነጠቁ።  አብዲሳ አጋ ሆሎታ ገነት ጦር ትምህርት ቤት ገብቶ ሥልጠናውን አጠናቋል። ሥልጠናውን እንዳጠናቀቀም የአሥር አለቃነት ማዕረግን አግኝቶ ተመርቋል። ይህንን ማዕረግ ካገኘ በኋላ  በ14 ዓመቱ የኢትዮጵያን ጦር በመቀላቀል ሀገሩን ማገልገሉን ሀ ብሎ ጀመረ። Sad and embittered, he joined the Ethiopian Army around the age of 14 and fought against Fascist Italy in 1936 in Ethiopia. He was captured and imprisoned in a concentration camp in the island of Sicily in Italy as stated in the next two paragraphs. በ1928 ጣልያን ኢትዮጵያን ስትወር ገና የ 16 ዓመት ጎረምሳ ነበር። አብዲሳ ጦሩን ከተቀላቀለ ከሁለት አመት በኋላ የአድዋን ሽንፈት ለመበቀል የዛተው ፋሺስት ሙሶሎኒ በድጋሚ ኢትዮጵያን ሲወር ሀገሩን ለመከላከል በ16 ዓመቱ ወራሪውን ጦር መዋጋት ጀመረ።  


ውጊያ ላይ ባጋጠመው የመቁሰል አደጋ ህክምና ላይ ከቆየ በኋላ አዲስ አበባ ውስጥ ፒያሳ አካባቢ በሚገኝ ቤት በቁም እስር ላይ ነበር። በኋላ ጣልያን ኢትዮጲያን እንዲያስተዳድር በሾመችው ግራዚያኒ ላይ የመግደል ሙከራ ከተደረገ በኋላ አብዲሳ አጋ እና ሌሎች 37 የሚሆኑ የቁም እስረኞች ተጠርጣሪ ተብለው በከባድ ስቃይ እስር ቤት ከቆዩ በኋላ በወቅቱ የጣልያን ግዛት በነበረችው በሶማሊያ በኩል ወደ ጣልያን ተወስዶ በሲሲሊ ደሴት በሚገኝ እስር ቤት እስረኛ ተደረገ።

አልሸነፍ ባይነት መለያው የሆነው አብዲሳ ጁሊዮ ከተባለ ዩጎዝላቪያዊ የጦር እስረኛ ጋር በመተባበር ከባድ ጥበቃ ከሚደረግበት እስር ቤት ለማምለጥ ማሰላሰል ጀመረ። ተሳክቶለት ቢያመልጥ እንግዳ አገር እንደሚጠብቀው ቢያውቅም በነጻነቱ የማይደራደረው አብዲሳ የተሰጠውን የብርድ-ልብስ ቀዳዶ በመቀጣጠል በመስኮት በኩል አመለጠ። 


ከዛ በኋላ ግን ሽሽት አልነበረም የጀመረው አብዲሳ። ከጥቂት ቀናት በኋላ በማታ ወደ እስር ቤቱ በመመለስ ጠባቂዎቹ ላይ ጥቃት በመፈጸም እስረኞቹን በመሉ ነጻ ማውጣት ችሎ ነበር። ያመለጡት እስረኞች ከእስር ቤቱ ጠባቂዎች በወሰዱት መሳሪያ በመታገዝ የአማጽያን ጦር ያደራጁ ሲሆን ጦሩን እንዲመራም የመረጡት ጀግናውን አብዲሳን ነበር። ከዛም የተለያዩ የጣልያን ወታደራዊ ሠፈራዎች ላይ ጥቃት በመፈጸም ወራሪዎቹ ጣልያኖች ኢትዮጵያ ውስጥ ከነበረው የአርበኛ እንቅስቃሴ ያልተናነሰ ጥቃት በሀገራቸው ያጋጥማቸው ጀመር። 

በአብዲሳ ጦር እጅግ የተረበሹት ጣልያኖችም በርካታ ስጦታዎችን ቃል በመግባት ውጊያውን እንዲያቆም እና የነሱን ጦር እንዲቀላቀል ለምነውት ነበር። አብዲሳ ግን ከፋሺስት ሥርዓት ጎን እንደማይቆም በማስረገጥ ጥያቄውን ውድቅ አደርጎ ጣልያኖችን በሀገራቸው ማስጨነቅ ቀጠለ።

በወቅቱ እየተጋጋለ የመጣው የጀርመን ናዚ ሥርዓት ሁለተኛው የዓለም ጦርነትን ሲጀምር ፋሺስት ሙሶሎኒ ከጀርመኖች ጋር ሲያብር እንግሊዝ፣ ፈረንሳይ እና አሜሪካን ጨምሮ በርካታ የምዕራብ አገሮች የሕብረት ጦር መስርተው የሙሶሎኒን ጦር መውጋት ጀምረው ነበር። 

በወቅቱ ይህ የሕብረት ጦር የአብዲሳን ዝና በመስማታቸው ጣልያንን ለማዳከም ለአብዲሳ ጦር የቁሳቁስ ድጋፎች ማድረግ ጀመሩ። በድጋፉ በመጠናከር ፋሺስቱን ሰራዊት ማርበድበድ የቀጠለው አብዲሳ የጣልያን ጦር ተሸንፎ ዋና ከተማዋ ሮም በአሜሪካን እና እንግሊዝ የሚመራ ጦር እጅ ስር ከወደቀች በኋላ የሚመራቸውን ከተለያዩ አገር የወጡ ወታደሮች በሙሉ ክንዳቸው ላይ የኢትዮጲያን ባንዲራ እንዲያስሩ በማድረግ የሃገሩን ባንዲራ እያውለበለበ ሮም ከተማ ሲገባ በአለም አቀፉ ህብረት ጦር ትልቅ አቀባበል ተደርጎለት ነበር። 

ከዛም በኋላ ከተጨማሪ ወታደሮች ጋር በአለም አቀፉ ህብረት ስር የሚመራ ጦር መሪ በመሆን ጀርመንን ለማሸነፍ በሚደረገው የመጨረሻ ውጊያ ላይ ተሳትፎ ግዳጁን በሚገባ በመወጣት የኢትዮጲያን ባንዲራ ከእጁ ሳይለይ በርካታ የጀርመን ከተሞችን ነጻ ማውጣት ችሎ ነበር። ከጦርነቱ መገባደድ በኋላም የእንግሊዝ፣ የካናዳ እና የአሜሪካ መንግሥታት ጦራቸውን ተቀላቅሎ እንዲቀጥል በርካታ ጥቅማ ጥቅሞችን አቅርበውለት ነበር። አብዲሳ ግን ኢትዮጵያ ምንም ያህል ድሃ ብትሆንም ሕዝቡን እና መንግሥቱን ጥሎ እንደማይሄድ አስረግጦ በመናገር ጥያቄውን ሳይቀበል ቀረ።

ተቀላቀለን የሚለውን ጥያቄ ውድቅ ማድረጉ ያልተዋጠላቸው አንዳንድ የሕብረት ጦሩ አባላት ሁለተኛ የዓለም ጦርነት ካበቃ በኋላ በወንጀል ከሰው አብዲሳን እስር ቤት አስገብተውት ነበር። በኋላም እስሩ ወደ ገንዘብ ቅጣት ተቀይሮ ገንዘቡ ተከፍሎ አብዲሳ ለዓመታት ወደተለያት ሀገሩ በክብር ተመለሰ። ከዛም ቀዳማዊ ኃይለ ሥላሴ በክብር ከተቀበሉት በኋላ በጊዜው የመከላከያ ሚኒስቴር ወደነበሩት ራስ አበበ አረጋይ መርተውት ነበር። 

ሚኒስቴሩ ውደመሩት ወደ ሆለታ ወታደራዊ ሠፈር የገባው አብዲሳ አነስ ባለ ወታደራዊ ቦታ የተወሰነ ጊዜ ከቆየ በኋላ ለጉብኝት የሚመጡ የውጭ ሀገር የጦር መሪዎች ስለ ዝናው ሲያወሩ የሰሙት ቀዳማዊ ኃይለ ሥላሴ ወደ ቤተ መንግሥታቸው በማምጣት በኮሎኔልነት ማዕረግ የንጉሡ ጠባቂ ሆኖ አድርገው ሾሙት። እስከ ንጉሣዊ ሥርዓቱ መውደቅ ድረስ በቦታው ያገለገለው አብዲሳ ከጥቂት ዓመታት በኋላ ከዚህ ዓለም በሞት ተለይቷል።

ለበለጠ መረጃ ከዚህ በታች የተያያዘውን የቅጅ ምስል በመመልከት የዚህንን ድንቅ ጀግና ታሪክ  ይወቁ 👇👇👇

አዘጋጅ፦ የታሪክ ክፍል 


የአማራ ትስስር በቻይና

መስከረም  5   2015 ዓ.ም 

ቻይና

የአማራ ትስስር በቻይና(ANiC)

የአማራ ሕዝብ የሚያኮራ ታሪክ፣ ቋንቋ፣ ስነጽሑፍ፣ ሃይማኖትና ባህል ያለው፤ የተፈጥሮ እና ሰው ሰራሽ ቅርሶች ባለቤት የሆነ፤ ሃገር የሰራ፣ ነጻነቱን ያስጠበቀ፤ የራሱ የሆነ ፊደል ያለው፤ የጥንታዊ ትምህርት ስርዓት ባለቤት የሆነ ጀግናና ኩሩ ሕዝብ ነው። የአማራ ሕዝብ በሃገረ መንግስት ምስረታ ሃገርን ከወራሪ መጠበቅና ዳር ድንበሯን በማስጠበቅ ታላቅ ገድል በመስራት እኛ ልጆቹ ቀና ብለን እንድንሄድ አድርጎናል።

Post a Comment

ቀዳሚ ገጽ ተከታይ ገጽ
hi