ይህ የአማራ ትሥሥርር በቻይና ይፋዊ ድረ-ገጽ ነው። በዚህ ድረ-ገጽ የአማራን ሕዝብ ታሪክ፣ ሃይማኖት፣ ባሕል፣ ልማድ፣ አርበኝነት፣ ቅርስ እና ሌሎች ተዛማጅ ጉዳዮችንም ጭምር ለአባላት በሚገባ እናሳውቃለን። የድረ-ገጹ ዋና አላማ የአማራን ታሪክ በሚገባ ለሁሉም በማስተማር ታሪካችንን ወደቀደመ ልዕልናው መመለስ ነው። አንድ አማራ ለሁሉም አማራ፤ ሁሉም አማራ ለአንድ አማራ፤ አንዲት ነጻ ሃገር ኢትዮጵያ -->

Seble Wongel

እቴጌ ሰብለ ወንጌል(1482- 1560ዓ.ም)

እቴጌ ሰብለ ወንጌል በ1482 ዓ.ም ተወለደች።  ሰብለ ወንጌል የዓፄ ልብነ ድንግል ሚስት ስትሆን ከንግሥት እሌኒ ሞት በኋላ በኢትዮጵያ ውስጥ ከፍተኛ ቦታ የነበራት ሴት መሪ ናት። የነበረችበት ዘመን፣ የአህመድ ግራኝ ጦር በቱርክ ጠመንጃ አንጋቢወች ታግዞ ብዙ የኢትዮጵያን ክፍል የተቆጣጠረበት ወቅት ነበር። She is well-known as a key political and military figure during the Ethiopian–Adal war, as well as the reigns of her sons and grandson. ግራኝ አሕመድ አፄ ልብነ ድንግልን ለአስራ ሁለት ዓመታት ያህል ያሳድድ በነበረበት ወቅት ባለቤቱ እቴጌ ሰብለ ወንጌል በዚያ ክፉ ጊዜ ከአጠገቡ አልተለየችም፤ አብራውም ትንከራተት  በዚህ የጦርነት ዘመን የመጀመሪያ ልጇ ፊቅጦር ሲገደል አራተኛው ልጇ ( የወደፊቱ አጼ ሚናስ ) በምርኮ ወደ የመን ተግዞ ነበር። የግራኝ ማሳደድ ሲበረታ አፄ ልብነ ድንግልና እቴጌ ሰብለ ወንጌል ትግራይ ደብረ ዳሞ ገዳም ገብተው ዋሻ ውስጥ ተደብቀው ነበር።  የደብረ ዳሞ ገዳም ተራራ ላይ የሚገኝ፣ በገመድ እየተጎተቱ የሚወጣበት፣ አንድ በር ብቻ ያለው በመሆኑ የግራኝ ጦር እዚያ ገዳም መግባት ባለመቻሉ ተስፋ ቆርጦ መመለሱ ይነገራል።  አፄ ልብነ ድንግል ደብረ ዳሞ በእፎይታ እየኖረ ሳለ እ.ኤ.አ በ1540 ዓ.ም በተፈጥሮ ህመም ከዚህ ዓለም በሞት ተለይቷል። እቴጌ ሰብለ ወንጌል ባለቤቷ ከሞተ በኋላ እዚያው ደብረ ዳሞ ተራራ ላይ ለአንድ ዓመት እጅ ሳትሰጥ በግራኝ ጦር ተከባ በተቀመጠችበትና ሁለተኛ ልጇ አጼ ገላውዲወስ አባቱን ተክቶ ንጉሥ ከሆነ በኋላ በተለያዩ የጦር ግንባሮች ውጊያ ከፍቶ ከግራኝ ጦር ጋር በመዋጋት ላይ እያለ በክሪስቶፈር ደጋማ የሚመራው የፖርቹጋል ጦር ምፅዋ መድረሱ ተሰማ። >

                              እቴጌ ሰብለ ወንጌል
ይህንን ዜና ስትሰማ ደብረ ዳሞ ተራራ ላይ ከሚገኘው ምሽጓ ላይ ሆና ከፖርቹጋሎቹ ጋር በመልእክተኛ አማካይነት በመነጋገርና በመደራደር ጠላት አለመሆናቸውን ካረጋገጠች በኋላ ከፖርቹጋሎቹ የጦር ኃይል ጋር ተቀላቀለች ከበቅሎዋ ላይ ቁጭ ብላም የፖርቹጋሎቹ 400 ውታደሮች በፊቷ ሲያልፉ ትመረምር እንደነበር ታሪክ ያትታል። የፖርቹጋሎቹ አራት መቶ (400) ወታደሮች እሷ ወዳለቺበት መጥተው በፊቷ በሰልፍ ሲያልፉ በቅሎ ላይ ሆና ትመለከት እንደነበርም የታሪክ ሰነዶች ላይ ሰፍሯል። በኋላም ከነበረችበት የተራራ ምሽግ ወርዳ ከፖርቹጋል ጦር ጋር ሆና የግራኝን ጦር እስከመጨረሻው ታግላ አታግላለች። 

የንግስቲቷን ድጋፍ ተከትሎ የአካባቢው ህዝብ ለፖርቹጋሎቹ ምግብና እርዳታ እንዳደረገ፤ ብዙወችም ይህን ሰራዊት እንደተቀላቀሉ ይነገራል። ቁስለኛውን በማከም፣ የለበሰችውንም ጥምጣም በመቅደድ ባንዴጅ በመስራት፣ ለሞቱትም በማልቀስ በጦር ውሎው ሁሉ ተሳታፊ ነበረች። በ1543 የክሪስታቮና ከደቡብ በኩል የመጣው የገላውዲወስ ሃይሎች ተገናኝተው በማበር አህመድ ግራኝን አሸነፍው ገደሉት። የግራኝ ሚስት ባቲ ድል ወምበሬ ብታመልጥም ልጇ መሃመድ ግን ተማርኮ ነበር። እ.ኤ.አ በ1543 የክሪስቶፈር ደጋማ ጦር እና ከደቡብ በኩል የመጣው የአፄ ገላውዲዎስ ሰራዊት ተገናኝተው አንድ ላይ በመሆን ወይና ደጋ በተባለ ስፍራ በተደረገ ውጊያ፣ ግራኝ አሕመድን አሸንፍው ሲገድሉት እቴጌ ሰብለ ወንጌል ያዝ!  በለው! እያለች እዚያው ጦርነት አቅራቢያ ላይ ነበረች። ባሏን አፄ ልብነ ድንግልን ለ12 ዓመታት ሲያሳድደው የነበረው ግራኝ አህመድንም ከባሏ ሞት በኋላ ኃይል አሰባስባና አስተባብራ በመዋጋት ለመበቀል ችላለች፡፡ የግራኝ ሚስት ባቲያ ድል ወምበራ ከመገደልና ከመማረክ ብታመልጥም ልጇ ሙሐመድ ግን በእነ እቴጌ ሰብለ ወንጌል ጦር ተማርኮ ነበር።

እቴጌ ሰብለ ወንጌል በጦርነት ተሳታፊ ብቻ ሳትሆን የሰላምና የዲፕሎማሲ አርበኛም ነበረች። ዚህም መሰረት ቀደም ሲል በግራኝ ጦር ተማርኮ ለግዞት ወደ የመን ተልኮ የነበረውን የልጇን የሚናስን (በኋላ አፄ ሚናስ የተባለው) ጉዳይ ለመፍታት ከባቲያ ድል ወምበራ (ከግራኝ ሚስት) ጋር በመልዕክተኛ አማካይነት የዲፕሎማሲ ግንኙነት በመፍጠር ለመወያየትና ለመደራደር ችላለች በእነ እቴጌ ሰብለ ወንጌልም በኩል የግራኝ ልጅ ተማርኮ ስለነበር ሁለቱ እናቶች ባደረጉት ድርድር የምርኮኛ ልውውጥ በማድረግ ልጆቻቸውን ከሞት አትርፈዋል። ሚናስ በዚህ ጊዜ ለቱርኩ መሪ ሱልጣን ሱሊማን በየመን ተልኮ ነበር። ይህ የተጋዘው ልጇ በድርድሩ መሳካት ምክንያት አይባ ላይ ከእናቱ ከሰብለ ወንጌል ሊቀላቀል ችሏል።

በምርኮ ልውውጥ የመጣው የሰብለ ወንጌል ልጅ ከስድስት ዓመት በኋላ ወንድሙ አፄ ገላውዲዎስ ድል ወምበራን ባገባው የግራኝ የእህት ልጅ በሆነው በአሚር ሙጃሂድ በጦርነት ሲገደል አፄ ሚናስ ተብሎ ስልጣን ላይ ወጣ። እቴጌ ሰብለ ወንጌል ለሚቀጥሉት አራት ዓመታት፣ እንደ ንግሥት እሌኒ በሐበሻ ማዕከላዊ የመንግሥት አስተዳደር ውስጥ ከፍተኛ ተሰሚነትን አግኝታ ነበር። ቀጥሎም በካቶሊክ እና በኦርቶዶክስ ሃይማኖት መካከል በተነሳው ሽኩቻ የኦርቶዶክስ ሃይማኖትን በመደገፍ በጽናት ቆማለች። ይሁንና በዚህ ምክንያት በተነሳው ጸብ የፖርቹጋል ካቶሊኮች ሊገደሉ ሲሉ በማማለድ ስራ ጉዳት እንዳይደርስባቸው አድርጋለች። ቤርሙዴዝ የተባለው ታውቂው የፖርቹጋል ተጓዥም ንጉሱን ገላውዲወስን በማናደዱ ከመገደል የተረፈው በሰብለ ወንጌል ተራዳኢነት ነበር። የስፔኑ ጀስዊት ፓትሪያርክ ኦቨዶም ከሞት የተረፈው በንግስቲቱ ምክንያት ነበር። ሠርፀ ድንግልን ወደ ሥልጣን እንዲወጣም ከጦረኞቹ በላይ ያገዘችው እናት ንግሥት ሰብለ ወንጌል ነበረች። ይህ ምርጫዋ የተሳካ ነበር ምክንያቱም ሰርጸ ድንግል ለ34 አመት ሲገዛ አገሪቱን በመከላከል ወደ ሰላም አሸጋግሯል።

የሰላምና የዲፕሎማሲ ባለሟል የነበረቺው እቴጌ ሰብለ ወንጌል፣ በአፄ ሠርፀ ድንግል ዘመነ መንግሥት በ1560 ዓ.ም አመድ በር በተባለ ቦታ ከዚህ ዓለም በሞት እንደተለየች የታሪክ ሰነዶች ያመለክታሉ።  እቴጌ ሰብለ ወንጌል ባለቤት የነበረው አፄ ልብነ ድንግል በህይወት በነበረበት ወቅት የራሱንና የሰብለ ወንጌልን ምስሎች ሠዓሊ በመቅጠር እንዲሳል ካደረገ በኋላ ግብፅ ወደ ሚገኘው ቅዱስ አትናቲዮስ ገዳም (st. antony monastery) እንዳስላከው በታሪክ መዝገብ ተመዝግቦ ይገኛል። በዚህ መጣጥፍ የተጠቀምንበት የእቴጌ ሰብለ ወንጌል ምስል የዚያ ቅጂ ከሆነ ቴምብር ላይ የተወሰደ ነው። የአጼ ልብነ ድንግል ምስል ከዚሁ ገዳም ይመነጫል።

አዘጋጅ፦ የታሪክ ክፍል 


የአማራ ትስስር በቻይና

መስከረም  4   2015 ዓ.ም 

ቻይና

የአማራ ትስስር በቻይና(ANiC)

የአማራ ሕዝብ የሚያኮራ ታሪክ፣ ቋንቋ፣ ስነጽሑፍ፣ ሃይማኖትና ባህል ያለው፤ የተፈጥሮ እና ሰው ሰራሽ ቅርሶች ባለቤት የሆነ፤ ሃገር የሰራ፣ ነጻነቱን ያስጠበቀ፤ የራሱ የሆነ ፊደል ያለው፤ የጥንታዊ ትምህርት ስርዓት ባለቤት የሆነ ጀግናና ኩሩ ሕዝብ ነው። የአማራ ሕዝብ በሃገረ መንግስት ምስረታ ሃገርን ከወራሪ መጠበቅና ዳር ድንበሯን በማስጠበቅ ታላቅ ገድል በመስራት እኛ ልጆቹ ቀና ብለን እንድንሄድ አድርጎናል።

1 Comments

  1. የቴክኖሎጅ ክፍል በውነቱ ጥሩ እየሰራችሁ ነው። በርቱ!!!

    ReplyDelete
ቀዳሚ ገጽ ተከታይ ገጽ
hi