ይህ የአማራ ትሥሥርር በቻይና ይፋዊ ድረ-ገጽ ነው። በዚህ ድረ-ገጽ የአማራን ሕዝብ ታሪክ፣ ሃይማኖት፣ ባሕል፣ ልማድ፣ አርበኝነት፣ ቅርስ እና ሌሎች ተዛማጅ ጉዳዮችንም ጭምር ለአባላት በሚገባ እናሳውቃለን። የድረ-ገጹ ዋና አላማ የአማራን ታሪክ በሚገባ ለሁሉም በማስተማር ታሪካችንን ወደቀደመ ልዕልናው መመለስ ነው። አንድ አማራ ለሁሉም አማራ፤ ሁሉም አማራ ለአንድ አማራ፤ አንዲት ነጻ ሃገር ኢትዮጵያ -->

አቡነ ዮሴፍ ተራራ( Pope Yosef mount)

አቡነ ዮሴፍ ተራራ  (የሳይንስና የቱሪዝም ማማ)

አቡነ ዮሴፍ ተራራ ወሎ(ቤተ-አማራ) ውስጥ ከላሊበላ በስተስሜን ምስራቅ የሚገኝ፤ ከኢትዮጵያ ከራስ ደጀን እና ከቱሉ ዲምቱ በመቀጠል በከፍታው 3ኛ የሆነ ተራራ ነው። ከባህር ወለል በላይ 4260 ሜትር የሚደርሰው ይህ ከፍተኛ ቦታ ከአካባቢው ጠለል ደግሞ በ1909 ሜትር ወደላይ ይጎናል።

አቡነ ዮሴፍ ደብር ከስር ይገኛል።  የሥነ ምህዳሩ ስያሜ መነሻውም ይህ ስፍራ ነው። የተከዜ ወንዝ ምንጭ የአቡነ ዮሴፍ ሥነ-ምህዳር ነው።  የዚህ ቦታ ስም የተወሰደው በ14ኛው መቶ ክፍለ ዘመን የዋሻ ውስጥ ቤተክርስትያን ሰርተው ይኖሩ ከነበሩ ታላቅ የሃይማኖት አባት( መነኩሴ) አቡነ ዮሴፍ ነው። አቡነ ዮሴፍ የበቁ አባት ናቸው። ሰው ከዝንጀሮ ጋር ሲጣላ፣ ዝንጀሮ ማሳ ሲያወድም አይተው ያስማሙ አባት ናቸው። ከስምምነቱ በኋላ ዝንጀሮ ዳርቻው ላይ እየጨፈረ ግን የማይደፍረው ማሳ ብዙ ነው። 

አቡነ ዮሴፍ የአካባቢውን ሰው ከዝንጀሮ ጋር አስማሙ ህዝቡ ቃርሚያ ለዝንጀሮው ሊለቅ፣ ዝንጀሮው ማሳ ገብቶ ላያወድም። ከአሥራ አራተኛው ክፍለ ዘመን ጀምሮ ዝንጀሮ ማሳውን የማይበላበት ገበሬ ሀገር የሆነው ምድር አናት ላይ ነኝ።

ይህ ቦታ በውስጡ የተለያዩ ማራኪ አገር በቀል እፀዋቶች አስታ፣ ጀበራ እንዲሁም ቀይ ቀበሮ፣ ጭላዳ ዝንጀሮ፣ ሰሳና ነብር ይገኛሉ። የአቡነ ዮሴፍ ተራራ  አየሩ እጅግ ይቀዘቅዛል። በሀገራችን ማህበረሰብ አቀፍ ጥብቅ ስፍራዎች አንዱ ለመሆን በቅቷል።  እጅግ አስደናቂ የሆነው የሰሜን ምሥራቅ ኢትዮጵያ ተራራ ነው። ብዙ ጊዜ በበረዶ ይሸፈናል። 

አቡነ ዮሴፍ በምድር ወገብ ላይ የሚገኝና ለስፔስ ሳይንስ ምርምር በአለም ላይ ተመራጭ ከሆኑ ቦታዎች አንዱ ነው። ክራውፎርድ የተባለዉ እንግሊዝ የአርኪዮሎጂ ተማሪ የጨረቃ ተራራ ተብሎ በጥንቶቹ ግሪኮችና አረቦች የሚታወቀው ጀበል ኤል-ካማር ይህ ተራራ እንደነበር ያስረዳል ። የጨረቃ ተራራ (ጀበል ኤል ካማር) በኋላ ኢኩየተር በመባል ለ ምድር ወገብ ስሙን የለገሰ ሐረግ ነው።


በዚህ ምክንያት የኢትዮዽያ ስፔስ ሳይንስ ሶሳይቲ (Ethiopian Space Science Society) ባረገዉ አለማቀፍ ጥናት ከአዲስ አበባ (እንጦጦ ተራራ) ቀጥሎ ሁለተኛዉን ስፔስ  አቡነ ዮሴፍ ተራራ የሳይንስና የቱሪዝም ማማ ሆኗል። ዛሬ ያልተነካና ድንግል አስደማሚ የተፈጥሮ እና ባህላዊ ቅርሶች እና አስደናቂ ስፔስ ሳይንስ የቴክኖሎጂ ውጤቶት (አዲስ አበባ እኳን የማይገኝ በጣም ፈጣን ኢንተርኔትን ጨምሮ) መገኛ ሆኗል። በአጠቃላይ አቡነ ዮሴፍ የጠፈር ምርምር እንዲሆን ከመጀመሩም በተጨማሪ ታሳቢ ጥብቅ ቦታ እንዲሆን መንግስትና ፍራንክ ፈርት ዞሎጂካል ሶሳይቲ [ተጨማሪ] ጥረት በማድረግ ላይ ይገኛሉ። በመሆኑም የአካባቢው ነዋሪዎች ማለትም ወደብየ፣ ጠልፈጢት፣ እንጃፋትና አቡነ ዮሴፍ በአንድ ላይ በመሆን በቱሪዝሙ እኩል ተጠቃሚ እንዲሆኑ የአቡነ ዮሴፍ ጓሳ ግብረ ሀይል በሚል ስያሜ ተደራጅተው የተለያዩ አገልግሎቶችን ማለትም ምግብ፣ መጠጥ፣ አልጋና ትራንስፖርት በማዘጋጀት የአካባቢው ህብረተሰብ በቱሪዝሙ ተጠቃሚ እንዲሆን በመንቀሳቀስ ላይ ይገኛሉ

ከተራራው በስተሰሜን ምሥራቅ ግርጌ ላይ የዋሻ ውስጥ የቅዱስ ገብርኤል ቤተ-ክርስቲያን ይገኛል። በዚህም ምክንያት ቱሪስቱ የተፈጥሮ መስህቡንና የዋሻ ውስጥ ቤተ-ክርስቲያኑን ለማየት የሀገር ውስጥና የውጭ ሀገር ዜጎች በየጊዜው ወደ ቦታው ይጓዛሉ አቡነ ዮሴፍ ተራራ መቼና መድኃኔ አለምንይምርሃነ ክርስቶስንጀመዱ ማርያምንገነተ ማርያምንአሸተን ማርያምን እና ሌላ አንድ የአለት ፍልፍል አብያተ ክርስቲያናንን በማቀፍ በታሪክ ይታወቃል። በአቡነ ዮሴፍ ተራራ ላይ በተደረገ ጥናት የ43 አይነት አጥቢ እንስሳት መኖሪያ መሆኑ ሲረጋገጥ፣ 221 አይነት ወፎችም ቤታቸው አድርገው ይኖሩበታል። ኢትዮጵያ ውስጥ ብቻ የሚገኙት ጭላዳ ዝንጀሮ እና ቀይ ተኩላ በዚሁ ቦታ ይገኛሉ። አቡነ ዮሴፍ ኢትዮጵያ ውስጥ ከሚገኙ የአዕዋፍ መኖሪያዎች በወፍ ሃብቱ ሁለተኛ ነው።



                አቡነ ዮሴፍ ተራራ በምስል 

በውበቱና በግርማዉ ልብ የሚነሽጠዉ አቡነ ዮሴፍ ተራራ በቅርበትና በዙሪያው ሌሎች ታሪካዊና የቱሪስት ቦታዎች ይገኛሉ።  
ከነዚህም፦  

          💫ግሸን ደብረ ከርቤ 73 ኪሜ ርቀት ላይ፣ 

          💫 የመቅደላ አምባ 90 ኪሜ ፣ 

         💫 የራስ ዳሽን ተራራ ቁንጮ 149 ኪሜ፣ 

         💫 ቡኃይት 160 ኪሜ፣ 

         💫 ሰይጣን መጣያ 178 ኪሜ፣

         💫 ጃናሞራ ተራራ 179 ኪሜ፣ 

         💫 ሊማሊሞ 181 ኪሜ፣

         💫 ማይለኃም ተራራ 188 ኪሜ፣

         💫  አባ ገሪማ ተራራ 226 ኪሜ፣

         💫  እምባ ሰለዳ 229 ኪሜ እና ሌሎችም ይገኛሉ።

ዐፄ ይኩኖ አምላክ በ12ኛው መክዘ በላሊበላ አቅራቢያ የጨረቃ ተራራ በመባል በሚታወቀው አቡነ ዮሴፍ ተራራ ላይ ቋጥኝ አስፈልፍለው ያሳነጿት ገነተ ማርያም የምትባል ቦታ አለች። ገነተ ማርያም ደጇፏ ላይም የይኩኖ አምላክ ፊርማ እና የእጅ ጽሑፋቸው ይገኛል።

[የግርጌ ማስተዋሻ፦ ግንቦት 19 ቀን የፃድቁ አቡነ ዮሴፍ የእረፍት ቀን በዚሁ ቦታ በድምቀት ይከበራል]

አዘጋጅ፦ የታሪክ ክፍል 


የአማራ ትስስር በቻይና

ጳጉሜ 1 2014 ዓ.ም 

ቻይና




የአማራ ትስስር በቻይና(ANiC)

የአማራ ሕዝብ የሚያኮራ ታሪክ፣ ቋንቋ፣ ስነጽሑፍ፣ ሃይማኖትና ባህል ያለው፤ የተፈጥሮ እና ሰው ሰራሽ ቅርሶች ባለቤት የሆነ፤ ሃገር የሰራ፣ ነጻነቱን ያስጠበቀ፤ የራሱ የሆነ ፊደል ያለው፤ የጥንታዊ ትምህርት ስርዓት ባለቤት የሆነ ጀግናና ኩሩ ሕዝብ ነው። የአማራ ሕዝብ በሃገረ መንግስት ምስረታ ሃገርን ከወራሪ መጠበቅና ዳር ድንበሯን በማስጠበቅ ታላቅ ገድል በመስራት እኛ ልጆቹ ቀና ብለን እንድንሄድ አድርጎናል።

Post a Comment

ቀዳሚ ገጽ ተከታይ ገጽ
hi