ይህ የአማራ ትሥሥርር በቻይና ይፋዊ ድረ-ገጽ ነው። በዚህ ድረ-ገጽ የአማራን ሕዝብ ታሪክ፣ ሃይማኖት፣ ባሕል፣ ልማድ፣ አርበኝነት፣ ቅርስ እና ሌሎች ተዛማጅ ጉዳዮችንም ጭምር ለአባላት በሚገባ እናሳውቃለን። የድረ-ገጹ ዋና አላማ የአማራን ታሪክ በሚገባ ለሁሉም በማስተማር ታሪካችንን ወደቀደመ ልዕልናው መመለስ ነው። አንድ አማራ ለሁሉም አማራ፤ ሁሉም አማራ ለአንድ አማራ፤ አንዲት ነጻ ሃገር ኢትዮጵያ -->

No title

ህዳር 13 ቀን 1967 ዓ.ም
ንጉሣዊውን ሥርዓት ገርስሶ በመጣል ሥልጣኑን የተቆጣጠረው የደርግ ሥርዓት የዘውዳዊውን መንግስት ከፍተኛ የጦርና የሲቪል ባለሥልጣናት በቁጥጥር ስር ማዋል ጀመረ። ደርግ በንጉሣዊው ሥርዓት ውስጥ በተለያዩ የሥልጣን ደረጃዎች ላይ ሆነው ሲያገለግሉ የነበሩትን በመቶዎች የሚቆጠሩ ባለሥልጣናት በቁጥጥር ስር እያዋለ ማሰር ሲጀምርም ባለሥልጣናቱ ከሕግ አግባብ ውጪ በዜጎች ላይ የፈጠሩአቸው ችግሮች እየታዩና እየተጣሩ እርምጃ እንደሚወሰድባቸውም ቃል ገብቶ ነበር፣
ከ60ዎቹ የደርግ ሰለባ ባለሥልጣናት መካከል የመጀመሪያውን የሞት ጽዋ የቀመሱት በውጊያ ብቃታቸው የተከበረና ገናና ስም የነበራቸውና ኮዳ ትራሱ በሚል የቅጽል ስም ይታወቁ የነበሩት ጀኔራል አማን ሚካኤል አምዶም ነበሩ። ጀኔራል አማን በኮሪያ ጦርነት ወቅት ኢትዮጵያ ላዘመተችው ሰራዊት አዛዥ ሆነው አመራር መስጠታቸውም ይታወሳል። ኅዳር 13/1967 ዓ.ም ኮሎኔል መንግስቱ ጀነራል አማንን በቁጥጥር ስር አውለው ወደ ደርግ ጽ/ቤት ይዘዋቸው እንዲመጡ ለወታደሮች ትዕዛዝ ሰጡ። ይህንን ትዕዛዝ የተቀበሉት ወታደሮችም ጀኔራሉን አስረው  ለማምጣት ቢሄዱም እንዳሰቡት አልተሳካላቸውም። ከተጧጧፈ የተኩስ ልውውጥ በኋላ ጀኔራሉ ሞቱ።

በማግስቱ ማለትም ህዳር 14/1967 ዓ.ም ደርግ በቁጥጥር ስር ባዋላቸው 59 የንጉሡ ስርዓት ባለሥልጣናት ሕይወት ላይ ውሳኔ ለመስጠት ተሰበሰበ። ደርግ በወቅቱ በቁጥጥር ስር ባዋላቸው ባለሥልጣናት ላይ አቅርቧቸው ከነበረው ክሶች መካከል በአስራ ሰባቱ የንጉሱ ሥርዓት ከፍተኛ ባለሥልጣናት ላይ ከሕግ አግባብ ውጪ ኃይል መጠቀም በሚል ወንጀል ክስ የቀረበባቸው ሲሆን በወታደራዊ መኮንኖቹ ላይ ደግሞ ስልጣንን መከታ በማድረግ ከሕግ አግባብ ውጪ ስልጣንን መጠቀም፣ የእርስ በእርስ ጦርነት ለማነሳሳት ደባ መፈፀምና ታላቁን የኢትዮጵያን የአመጽ እንቅስቃሴ ለማዳፈን መሞከር እንዲሁም የገቡትን ቃል ኪዳን ማጠፍና በወታደሩ መካከል ልዩነት መፍጠር የሚሉት ይገኙበታል። ደርግ በእነዚህ ወንጀሎች ክስ መስርቶ በቁጥጥር ስር ያዋላቸውን የንጉሣዊ አስተዳደር መንግስት ባለሥልጣናት ጉዳይ ላይ ውሳኔ ለመስጠት ሲሰበሰብም እዛው የደርግ ከፍተኛ ባለሥልጣናቱ በተሰበሰቡበት አዳራሽ ምድር ቤት ውስጥ እስረኛ ባለሥልጣናቱ ይገኙ ነበር። 
የንጉሣዊው ሥርዓት ከፍተኛ ባለሥልጣናትና ወታደራዊ መኮንኖቹ ላይ የሞት ቅጣት ውሳኔው በተላለፈበት ወቅት ውሳኔውን ከደርግ ባለሥልጣናት መካከል ኮሎኔል ብርሃኑ ባይህ በጥብቅ ተቃውመውት እንደነበር ሻምበል ፍቅረ ስላሴ ወግደርስ “እኛና አብዮቱ” በተሰኘው መጽሐፋቸው ላይ ገልጸውታል ውሳኔው የአብዛኛውን የደርግ ባለሥልጣናት ይሁንታ አግኝቶ ተግባራዊ ከተደረገ በኋላ ማምሻውን ደርግ እንዲህ የሚል መግለጫ አወጣ። ምክር ቤቱ (ደርግ) የተለያዩ ሸረባዎችን በማድረግ አገሪቱ በደም አበላ እንድትታጠብ ተደጋጋሚ መሰሪ ተግባራትን የፈፀሙትን የቀድሞዎቹን የሲቪልና ወታደራዊ ባለሥልጣኖች በሞት መቅጣት አስፈላጊ ሆኖ አግኝቶታል። ይህ ውሳኔ ባለፉት ጊዜያት በከፍተኛ ደረጃ ሲሰቃዩ የቆዩትን ምንም አይነት ወንጀል የሌለባቸውን ንጹሐን ዜጎችን ሕይወት ለመታደግ ሲባል የተደረገ ነው። ስለሆነም ምክር ቤቱ (ደርግ) በመጥፎ አሰራራቸው ጥፋተኛ ሆነው በተገኙት ፍትህ እንዲስተጓጎል ደንቃራ ሲሆኑ በቆዩት የአገሪቱን ሰነድ ምሥጢር ለውጪ ወኪሎች በሸጡና በአሁኑ ጊዜ እየተካሄደ ያለውን የኢትዮጵያን ታላቁን የለውጥ እንቅስቃሴ ለማደናቀፍ በተሰለፉት ሰዎች ላይ የሞት ቅጣት ሰጥቷል።  በወቅቱ ሁኔታው በዜጎች ላይ የፈጠረው ድንጋጤ ከፍተኛ ነበር። በዚህ የደርግ ውሳኔም ህይወታቸውን ካጡት ታላላቅ ባለስልጣት መካከል አክሊሉ ሀብተወልድ፣ ልጅ እንዳልካቸው መኮንን፣ ራስ መስፍን ስለሺ፣ ልዑል አስራተ ካሣ፣ ደጃዝማች ለገሰ ብዙ፣ ደጃዝማች ከበደ አሊ እና አፈንጉስ አበጀ ደባልቅ እና ሌሎችም ይገኙበታል። ይህ ድርጊት ከተፈፀመ እነሆ ነገ ዛሬ ሕዳር 14 2015  አርባ ስምንተኛ ዓመቱን ይዟል። እነዚህ የደርግ ሰለባ የቀድሞ የዘውዱ ሥርዓት ታላላቅ ባለሥልጣናት ከተቀበሩበት የጅምላ መቃብር አጽማቸው ተቆፍሮ እንዲወጣና በክብር እንዲያርፍ ተደርጓል። ሙሉ ደብዳቤው እንደሚከተለው በጽሑፍ ቀርቧል።


ከ48 ዓመት በፊት ልክ በዛሬዋ ቀን ጊዜያዊ የወታደራዊው የደርግ መንግስት አባላት በቀድሞዎቹ የቀ.ኃ.ሥ ስልሳዎቹ ባለሥልጣናት እንዲገደሉ በወሰኑት ውሳኔ መሠረት ፤ ትዕዛዙ እንዲፈፀም ምክትል ሊቀመንበሩ ሻለቃ መንግስቱ ኃይለማሪያም በፊርማቸው ያፀደቁበት ዕለት ነበር።

ለደርጉ የዘመቻና ጥበቃ መምሪያ መኮንን አዲስ አበባ።
                ጉዳዩ:- በቀድሞ የመንግሥት ባለሥልጣናት ላይ የተላለፈውን ከፍተኛ የፓሊሲ ውሳኔ ተግባራዊ ስለማድረግ ይመለከታል።

በአገራችን በፊውዳሉ አስከፊ ሥርዓት ላይ ተቀጣጠለውን ሕዝባዊ አብዮት መርቶ ከግቡ ለማዳረስ ግንባር ቀደም ኃላፊነቱን የወሰደው ከጭቁኑ መለዮ ለባሽ የተውጣጣው አብዮታዊ ደርግ የአገሪቱን ሥልጣን ተረክቦ በመምራት ላይ ይገኛል። አብዮታዊ ደርግ ከተቋቋመበት ጊዜው ጀምሮ የዘውድ አገዛዝን ከማስወገድ አልፎ የ ቀ.ኃ.ሥ ባለስልጣናትን በቁጥጥር ስር አውሎ ጉዳያቸውን ሲያጠና የቆየ መሆን ከነዚህም መካከል ላለፉት 40 ዓመታት ጭቁኑን የኢትዮጵያ ሕዝብ ሲረግጡና ሲመዘበሩ የነበሩ ከፍተኛ የሲቪልና ወታደራዊ ባለስልጣናት ላይ ከፍተኛ የፖለቲካ ውሳኔ አስተላልፏል። ሰሞኑን የደርግ አባላት ባደረጉት ከፍተኛ ስብሰባ በአንደኛ ዙር የስም ዝርዝራቸው ከዚህ ትዕዛዝ ጋር የተያያዘው የቀድሞ ባለሥልጣናት ላይ አብዮታዊ እርምጃ እንዲወሰድባቸው ሙሉው የደርግ አባላት በአንድ ድምፅ ወስኖዋል። 
 ትዕዛዝ ---------
1ኛ. ሌ/ጄነራል አማን አምዶም ከመኖሪያ ቤታቸው በቁጥጥር ስራ ውለው ወደ ቤተመንግስት በማምጣት ከእስረኛችን እንዲቀላቀሉ ፣ 2ኛ.በዋናው ከርቸሌ ለ54 ሰው በዶዘር ጉድጔድ እንዲቆፈር ሆኖ ከተራ ቁጥር አንድ እስከ 54 ያሉት ከፍተኛ የሲቪልና የጦር ባለሥልጣናት ከምሽቱ ሁለት ሰዓት ከእስረኛች ተለይተው ለብቻ እንዲቆዮ።
3ኛ. ከሌሊቱ 8:00 /2፡00/ ሰዓት በወታደራዊ መኪናዎች ወደ ዋናው ከርቸሌ ተወስደው በአንድ ላይ በጥይት ተደብድበው እንዲገደሉ እናስታውቃለን። በማግስቱም ኅዳር 14 ቀን 1967 ዓ.ም የቀዳማዊ ኃይለሥላሴ ከፍተኛ ባለስልጣናት እጅግ በሚያሳዝን መልኩ በጥይት ተደብድበው ተገደሉ።
የአማራ ትስስር በቻይና(ANiC)

የአማራ ሕዝብ የሚያኮራ ታሪክ፣ ቋንቋ፣ ስነጽሑፍ፣ ሃይማኖትና ባህል ያለው፤ የተፈጥሮ እና ሰው ሰራሽ ቅርሶች ባለቤት የሆነ፤ ሃገር የሰራ፣ ነጻነቱን ያስጠበቀ፤ የራሱ የሆነ ፊደል ያለው፤ የጥንታዊ ትምህርት ስርዓት ባለቤት የሆነ ጀግናና ኩሩ ሕዝብ ነው። የአማራ ሕዝብ በሃገረ መንግስት ምስረታ ሃገርን ከወራሪ መጠበቅና ዳር ድንበሯን በማስጠበቅ ታላቅ ገድል በመስራት እኛ ልጆቹ ቀና ብለን እንድንሄድ አድርጎናል።

Post a Comment

ቀዳሚ ገጽ ተከታይ ገጽ
hi