ይህ የአማራ ትሥሥርር በቻይና ይፋዊ ድረ-ገጽ ነው። በዚህ ድረ-ገጽ የአማራን ሕዝብ ታሪክ፣ ሃይማኖት፣ ባሕል፣ ልማድ፣ አርበኝነት፣ ቅርስ እና ሌሎች ተዛማጅ ጉዳዮችንም ጭምር ለአባላት በሚገባ እናሳውቃለን። የድረ-ገጹ ዋና አላማ የአማራን ታሪክ በሚገባ ለሁሉም በማስተማር ታሪካችንን ወደቀደመ ልዕልናው መመለስ ነው። አንድ አማራ ለሁሉም አማራ፤ ሁሉም አማራ ለአንድ አማራ፤ አንዲት ነጻ ሃገር ኢትዮጵያ -->

Gondar

 ➖ ጎንደር ➖




ጎንደር ማለት  ጉንደ ሀገር ከሚለው የግእዝ ቃል የተገኘ ሲሆን ትርጓሜውም የሀገር ግንድ፣ የሀገር መሠረት፣ ርዕሰ ሀገር ወይም የሀገር ራሥ ማለት ነው። ይኼውም  ኖኅ ከጥፋት ውኃ በኋላ የተቀመጠበት በእንተላ ፣በአይዋርካ፣ በሽሌ፣ በአይከል፣ በኩል አድርጎ ጎንደር ላይ ብዙ ዘመን ፈጣሪውን እያመሰገነ እየቀደሰ የኖረባትና የተቀበረባት ቦታ በመሇኗ የሀገር መጀመሪያ፣ ዋና ግንድ ተባለች። እንዲያውም  በ950 ዓ.ዓ ኖኅ ሲሞት መቃብሩ ላይ ምንጭ ፈልቆ በርካታ ሰዎችን ይፈውስ ነበር። ከዚያም ለኖኅ መታሠቢያ ይሆን ዘንድ አምላክ በቤተመንግሥት አሳቦ የኖኅ የመቃብር ሐውልት እንዲታነጽ ፈቀደ። ይህም በኋለኛው ዘመን በንጉሥ ፋሲለደስ የታነጸው የፋሲል ግንብ ነው።

ዐፄ ፋሲለደስም በ1629 ዓ.ም በመሐንዲስ አባ ገብረክርስቶስ  መሪነት የእደ ጥበብ ባለሙያዎችን በማሰባሰብ ከኖኅ መቃብር ላይ የቤተመንግሥቱን ታላቅ መሠረት ጥለውታል። ግንባታውም በሰባት ዓመት ውስጥ ተጠናቀቀ። ከዚህ በኋላ ዐፄ ፋሲል በቀሐ ወንዝ አጠገብ  ማንኪት የሚባለውን ሕንጻ በ17,000 (ዐሥራ በጸሰባት ሺህ) ካሬ ሜትር ስፋት ባለው ግቢ መሀል ላይ 50 ሜትር በ25 ሜትር ስፋትና 2 ሜትር ጥልቀት ያለው የባሕረ ጥምቀት ገንዳ አስገነቡ። ከቀሃ ወንዝ በተቆፈረ ቦይ ውኃ ተጠልፎ እንዲገባ አደረጉ። ከዛን ጊዜ ጀምሮ ገንዳው ለጥምቀት በዓል መጠመቂያነት የሚያገለግል ሲሆን፣ ዐፄ ፋሲል ባሠሩት ጥንታዊ ሕንጻ ደግሞ የታቦታቱ ማደሪያ ሆኖ ያገለግላል። መዋኛ ገንዳው በባእሉ ሰሞን የባንዲራ መቀነት ይታጠቃል፡፡

ጎንደር የመንግሥት ከተማ ከሆነችበት እስከ ጎንደር ዘመን ማክተሚያ ፈጻሜ መንግሥት አፄ ተክለ ጊዮርጊስ ድረስ 18 ነገሥታት የነገሱ ሲሆን እነዚህም አብዛኛዎቹ አብያተ ክርስቲያናትን አሠርተዋል። 44 የሚባሉት አብያተ ክርስቲያናት ጎንደር የመንግሥት ከተማ ከመሆኗ አስቀድሞ የተተከሉበትን ጨምሮ እስከ ፈጻሜ መንግሥት ተክለ ጊዮርጊስ ድረስ የተተከሉትን ብቻ ሲሆን ቁጥራቸውም 44 ነው። ከዚያ ወዲህ ከዘመነ መሣፍንት እስከ አሁን የተተከሉ በርካታ አብያተ ክርስቲያናት ቢኖሩም ከ44ቱ የሚቆጠሩ አይደሉም።  በአጠቃላይ አርባ አራቱ ታቦታት  በጎንደር ዘመን በጎንደር ከተማና አካባቢው የሚገኙና የነበሩ 44 አብያተ ክርስቲያናት ጥቅል ስም ነው፡፡ ይህም ማለት አሁን ባለው የጎንደር ከተማ ክልል እና ዙሪያውን በሚገኙ አዋሳኝ የገጠር ቀበሌዎች ለምሳሌ፣ ጠዳ፣ ፈንጠር፣ ብላጅግ፣ ደፈጫ እና በመሳሰሉት ቦታዎች የሚገኙ አጠቃላይ የአድባራት ቁጥር ነው፡፡


የአርባ አራቱታቦታት ስም ዝርዝር፦

 1-አዘዞ ተ/ሃይማኖት                   15-አደባባይ ተ/ሃይማኖት                                   29-ሰሖር ማርያም

2-ፊት አቦ                                16-ደብረ ብርሃን ሥላሴ                                      30-ወራንገብ ጊዮርጊስ 

3-ፊት ሚካኤል                         17-ዳረገንዳ ኤዎስጣቴዎስ                                   31-ምንዝሮ ተ/ሃይማኖት

4-አደባባይ ኢየሱስ                    18-አጣጣሚ ሚካኤል                                        32-ደ/ፀሐይ ቊስቋም

5-ግምጃ ቤት ማርያም                19-ጐንደር ሩፋኤል-                                          33-ደ/ምጥማቅ ማርያም

6-እልፍኝ ጊዮርጊስ                    20-ደፈጫ ኪዳነ ምህረት                                     34-አባ ሳሙኤል

7-መ/መ/መድኃኔዓለም               21-ቅ.ዮሐንስ መጥምቅ                                       35-ጐንደሮች ማርያም

8-አቡን ቤት ገብርኤል               22-ጐንደር ልደታ ማርያም                                   36-ጐንደሮች ጊዮርጊስ

10-አባ እንጦንስ                      23-ሠለስቱ ምዕት                                               37-አባ ጃሌ ተ/ሃይማኖት

9-ፋሲለደስ                            24-ጎንደር በአታ ለማርያም                                    38-ዐቢየ እግዚእ.ኪ/ምህረት

11-ጠዳ እግዚአብሔር አብ         25-ወ/ነጐድጓድ ዮሐንስ                                        39-ብላጅግ ሚካኤል

12-አርባዕቱ እንስሳ                  26-ጐንደር ቂርቆስ                                                40-አሮጌ ልደታ

13-ቀሐ ኢየሱስ                      27-ጐንደር ሐዋርያት(ጴጥሮስ ወጳውሎስ )                  41-ጫጭቁና ማርያም

14-አበራ ጊዮርጊስ                   28-ፈንጠር ልደታ                                                 42-ጋና ዮሐንስ

43-አይራ ሚካኤል                   44-ዳሞት ጊዮርጊስ


ምንጭ -  የኢትዮጵያ ታሪክ

አዘጋጅ፦ የታሪክ ክፍል


የአማራ ትስስር በቻይና

ጥቅምት 25  2015 ዓ.ም 

ቻይና

የአማራ ትስስር በቻይና(ANiC)

የአማራ ሕዝብ የሚያኮራ ታሪክ፣ ቋንቋ፣ ስነጽሑፍ፣ ሃይማኖትና ባህል ያለው፤ የተፈጥሮ እና ሰው ሰራሽ ቅርሶች ባለቤት የሆነ፤ ሃገር የሰራ፣ ነጻነቱን ያስጠበቀ፤ የራሱ የሆነ ፊደል ያለው፤ የጥንታዊ ትምህርት ስርዓት ባለቤት የሆነ ጀግናና ኩሩ ሕዝብ ነው። የአማራ ሕዝብ በሃገረ መንግስት ምስረታ ሃገርን ከወራሪ መጠበቅና ዳር ድንበሯን በማስጠበቅ ታላቅ ገድል በመስራት እኛ ልጆቹ ቀና ብለን እንድንሄድ አድርጎናል።

Post a Comment

ቀዳሚ ገጽ ተከታይ ገጽ
hi