እንኳን ለንጉሡ እምዬ ምኒልክ(ዳግማዊ ዓጤ ምኒልክ) ፻፸፰ ዓመት እና ንግሥቲቱ እቴጌ ጣይቱ ብጡል(ብርሐን ዘኢትዮጵያ) ፻፹፪ ዓመት የልደት በዓል አደረሳችሁ።
💫ዳግማዊ ዓጤ ምኒልክ ከአባታቸው ከሸዋው ንጉሥ ኃይለ መለኮት ሣህለ ሥላሴ እና ከእናታቸው ወይዘሮ እጅጋየሁ ለማ አድያም ቅዳሜ ነሐሴ 12 ቀን 1836 ዓ.ም ደብረ ብርሃን አካባቢ አንጎለላ ከሚባል ሥፍራ ተወለዱ።💫
ድሃ ከወደደበት ቦታ ይቀመጥ፤ በዘር በወገን ልዮነት አይከልከል። ዳግማዊ አጤ ሚኒሊክ
ምኒልክ ተወልዶ ባያነሳ ጋሻ ግብሩ እንቁላል ነበር ይህን ግዜ ሃበሻ።
እቴጌ ጣይቱ
💫እቴጌ ጣይቱ ብጡል ከአባታቸው ደጃዝማች ብጡል ኃይለ ማርያም እና ከእናታቸው ወይዘሮ የውብዳር ነሐሴ 12 ቀን 1832 ዓ.ም በጎንደር ውስጥ ደብረ ታቦር ከተማ ተወለዱ። ብርሃን ዘ ኢትዮጵያ በሚል ቅፅል ስም ይታወቃሉ።💫
ትውልድ ተጨንቆ አፈና ይዞት፣
ዓለም ተደሰተ ፀሐይ ወጣለት።
እኔ ሴት ነኝ ጦርነት አሎድም ኢትዮጵያን የጣሊያን የሚያደርጋት ውል ከመፈረም ግን ጦርነት እመርጣለው።
ዳግማዊ አጤ ምኒልክ እና እቴጌ ጣይቱ ብጡል
ታላቁን ጥቁር ሰው እምዬ ምኒልክን ለመዘከር በዓለም በሚገኙ ሀገራት የተሰየሙ መታሰቢያዎች
፩. በኬንያ ዋና ከተማ ናይሮቢ በምኒልክ ስም የተሰየመ መንገድ፣
፪. በለንደን ከተማ በምኒልክ የተሰየመ መንገድ፣
፫. በጅቡቲ በምኒልክ የተሰየመ ሆቴል፣
፬. በደቡብ አፍሪካ በምኒልክ የተሰየመ ሽቶ፣
፭. በቤልጂየም በምኒልክ የተሰየመ ቢራ፣
፮. በብራዚል በምኒልክ የተሰየመ ካፌ፣
፯. በብራዚል በምኒልክ የተሰየመ ጋዜጣ፣
፰. በፈረንሳይ በምኒልክ የተሰየመ ቸኮሌት ...ወዘተ ይገኛሉ።
[ሙሉ ታሪኩን በዚሁ ገጽ ላይ እናቀርባለን...]
እንኳን አብሮ አደረሰን! ታሪኩ ግን ይለቅልነ
ReplyDelete