ይህ የአማራ ትሥሥርር በቻይና ይፋዊ ድረ-ገጽ ነው። በዚህ ድረ-ገጽ የአማራን ሕዝብ ታሪክ፣ ሃይማኖት፣ ባሕል፣ ልማድ፣ አርበኝነት፣ ቅርስ እና ሌሎች ተዛማጅ ጉዳዮችንም ጭምር ለአባላት በሚገባ እናሳውቃለን። የድረ-ገጹ ዋና አላማ የአማራን ታሪክ በሚገባ ለሁሉም በማስተማር ታሪካችንን ወደቀደመ ልዕልናው መመለስ ነው። አንድ አማራ ለሁሉም አማራ፤ ሁሉም አማራ ለአንድ አማራ፤ አንዲት ነጻ ሃገር ኢትዮጵያ -->

Black Lion Hospital(ጥቁር አንበሳ ሆስፒታል)

 ጥቁር አንበሳ ሆስፒታል አገልግሎት መስጠት የጀመረው መቼ ነው?

💫ጥቁር አንበሳ ሆስፒታል ስራ (አገልግሎት መስጠት) የጀመረው ኅዳር 24 ቀን 1966 ዓ.ም ነበር።

ሆስፒታሉ ግንባታው ተጠናቆ በንጉሠ ነገሥት ግርማዊ ቀዳማዊ ኃይለሥላሴ የተመረቀው ጥቅምት 24 ቀን 1966 ዓ.ም ነበር። የሆስፒታሉ ግንባታ የተጀመረው በ1950ዎቹ መጨረሻ ላይ ሲሆን ግንባታው 21 ሚሊዮን 605 ሺህ 399 ብር ወጥቶበታል። 


የሆስፒታሉ የመጀመሪያ ስም የልዑል መኮንን መታሰቢያ ሆስፒታል ነበር። ልዑል መኮንን ወደ ናዝሬት/አዳማ ሲጓዙ መንገድ ላይ ባጋጠማቸው የመኪና አደጋ ምክንያት ሕይወታቸውን ያጡት የቀዳማዊ ኃይለሥላሴ ሁለተኛ ልጅ መሆናቸው ይታወቃል። 

ወታደራዊው ቡድን (ደርግ) ሥልጣን ከያዘ በኋላ የሆስፒታሉ ቀድሞ ስም ተቀይሮ ከ1968 ዓ.ም ጀምሮ  ጥቁር አንበሳ ሆስፒታል ተብሎ መጠራት ጀመረ። ጥቁር አንበሳ በፋሺስት ኢጣሊያ ወረራ ወቅት ከፍተኛ መስዋትነት የከፈሉትና በ1928 ዓ.ም የተመሰረተው የሆለታ ገነት የጦር ትምህርት ቤት የመጀመሪያዎቹ ምሩቆች የነበሩ ወጣት አርበኞች የትግል ስም ነው።  ሆስፒታሉ በዚህ ስም እንዲጠራ የተደረገው የእነዚያን ወጣት አርበኞች ጀግንነትና የአገር ፍቅር ስሜት እንዲታወስና ለትውልዶች እንዲተላለፍ ታስቦ እንደሆነ ይነገራል። 

ጥቁር አንበሳሆ ስፒታል የተገነባው 500 አልጋዎች እንዲኖሩት ተደርጎ የነበረ ቢሆንም ስራ የጀመረው ግን በ150 አልጋዎች ብቻ ነበር። ዛሬ 67% ነጻ ሕክምና የሚሰጠው ሆስፒታሉ፣ ሲመሰረት 25 አልጋዎችን ነጻ ሕክምና ለሚሰጣቸው ችግረኞች መድቦ ነበር።

ሆስፒታሉ ስራ የጀመረው በኢትዮጵያና በስዊዘርላንድ መንግሥታት መካከል በተደረገ ስምምነት በሁለቱ አገራት የህክምና ባለሙያዎች ጥምረት በ18 ሐኪሞች ሲሆን ከእነዚህ ሐኪሞች መካከል ስድስቱ ኢትዮጵያውያን ነበሩ። ከ25ቱ ነርሶች መካከል ደግሞ 12ቱ ኢትዮጵያውያን፣ 13ቱ ደግሞ የስዊዝ ነርሶች ነበሩ። በተጨማሪም 22 ኢትዮጵያውያን ድሬሰሮች ነበሩት።

የሆስፒታሉ አልጋዎች ሶስት ደረጃዎች ነበሯቸው። እነርሱም፦ 

1ኛ፦ አንደኛ ደረጃ አልጋ

2ኛ፦ ሁለተኛ ደረጃ አልጋ

3ኛ፦ ሦስተኛ ደረጃ አልጋ

አንደኛ ደረጃ አልጋ እንደክፍሉ ይዞታ ከ30 እስከ 50 ብር ይከፈልበታል። ለሁለተኛ ደረጃ አልጋ ደግሞ 12 ብር ይከፈል ነበር። በእነዚህ ሁለት የአልጋ ክፍሎች የሚታከሙ ታካሚዎች ለሚያገኙት የህክምና አገልግሎት ተጨማሪ ክፍያ ይፈጽማሉ። ሦስተኛ ደረጃ አልጋ ክፍል ግን ለየትኛውም ዓይነት የህክምና አገልግሎትና ለአልጋው በድምሩ በቀን የሚከፈለው 10 ብር ነበር። ተመላላሽ ታካሚዎች ለምዝገባ የሚከፍሉት የሦስት ብር ክፍያ ሁሉንም አይነት የላብራቶሪ ምርመራ ጭምር የሚያካትት ነበር። 

በሁሉም ደረጃ የመኝታ ክፍሎች ውስጥ በእያንዳንዱ አልጋ አጠገብ የሬዲዮ ዜናዎችና ሙዚቃ ለመስማት ለሚፈልጉ ታካሚዎች ሁሉ ቴፖች ተዘጋጅተውላቸውም ነበር። ታዲያ የአንደኛው ፍላጎት የሌላውን ጸጥታ እንዳያውክ ለሁሉም ቴፖች የተዘጋጁ በጆሮ ላይ የሚደረጉ የማዳመጫ መሳሪያዎች ነበሩ።  💫

አዘጋጅ፦ የታሪክ ክፍል ከቴክኖሎጂ ክፍል ጋር በመተባበር

የአማራ ትስስር በቻይና

ነሐሴ 09 2014 ዓ.ም 

ቻይና

የአማራ ትስስር በቻይና(ANiC)

የአማራ ሕዝብ የሚያኮራ ታሪክ፣ ቋንቋ፣ ስነጽሑፍ፣ ሃይማኖትና ባህል ያለው፤ የተፈጥሮ እና ሰው ሰራሽ ቅርሶች ባለቤት የሆነ፤ ሃገር የሰራ፣ ነጻነቱን ያስጠበቀ፤ የራሱ የሆነ ፊደል ያለው፤ የጥንታዊ ትምህርት ስርዓት ባለቤት የሆነ ጀግናና ኩሩ ሕዝብ ነው። የአማራ ሕዝብ በሃገረ መንግስት ምስረታ ሃገርን ከወራሪ መጠበቅና ዳር ድንበሯን በማስጠበቅ ታላቅ ገድል በመስራት እኛ ልጆቹ ቀና ብለን እንድንሄድ አድርጎናል።

Post a Comment

ቀዳሚ ገጽ ተከታይ ገጽ
hi